ሀገሬ ቲቪ

የምርጫ ውጤት ወሳኙ የሽንኩርት ስጦታ

ታይዋን በየአራት አመቱ በምታካሂደው ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በቅስቀሳ ወቅት ከመራጮች የሚሰጥ የሽንኩርት ስጦታ መጠን ውጤት አመላክች ነው መባሉን ሰማን።

በሁሉም የአለማችን ክፍል የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ሲዎዳደሩ የፖለቲካ ሃስባቸውን እና ህዝቡ ያለበትን ችግር ተረድተው መፍትሄ ሊያመጡ እንደሚችሉ የተለያዩ ማሳያዎች በመጥቀስ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የተለመደ ነው።

ህዝቡም ታዲያ በምርጫ ዕለት ይበጀኛል ያስተዳድረኛል ለሚለው የፖለቲካ ፓርቲ ድምፁን ወረቀት ላይ በማስፈር በተዘጋጀለት የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ በማኖር ይሁንታውን ይሰጣል።

የታይዋን የፖለቲካ መሪዎች ግን የህዝቡን ይሁንታ ማግኘታቸውን የሚያውቁት ከምርጫው በፊት ገና በቅስቀሳ ወቅት ነው።

የየአካባቢው ተመራጮች ለቅስቀሳ ሲወጡ በመራጮቻቸው የተለያዩ የአትክልት አይነቶች ከተበረከተላቸው የመርጮቻችውን ይሁንታ አግኝተዋል ማለት ነው በተለይ ያትክልት ስጦታው ባሮ ሽንኩርት የሚሉት ከሆነማ የመራጮች ልብ አለልክ ተማርኳል ማለት ነው።

ታይዋን በኤዥያ ከሚገኙ ሃገራት እጅጉን ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ሃገር ናት፡፡ ይችው ዲሞክራሲያዊ ሃገር በየአራት አመቱ ሃያ ሶስት ሚሊዮን ህዝቦች የሚሳተፉበት ምርጫ ታከናውናለች፡፡

ታዲያ ከዚህ ምርጫ አስቀድመው ሃገሪቱን ለማስተዳደር እራሳቸውን ብቁ ያደረጉት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በህቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት አስቀድሞ ለማወቅ በቴሊቪዥኝ አልያም በየአደራሹ ከሚካሄድ ቅስቀሳና የፖለቲካ ክርክር ይልቅ የገበያ ስፍራን ይመርጣሉ።

በዚህ የገበያ ስፍራ ቅስቀሳ በረከት ያሉ የሽንኩርት ስጦታዎችን የተበረከተለት የፓርቲ መሪ እርሱም ሆነ ፓርቲው የምርጫውን ቀን የሚጠብቁት ውጤቱን ህጋዊ ለማድርግ እንጂ አሽናፊነት ወደ እርሱ እንዳደላች አስቀድሞ ያውቃል ።

በዚያው ልክ አትክልትና ፍራፍሬ የሚሰጠው ካጣ አልያም የሚሰጠው ስጦታ ከሽንኩርት ውጪ ከሆነም የማሸነፉ ነገር አጠራጣሪ ነው ።

ህዝቡ በፓርቲው አልያም በግለሰቡ ላይ እምነት የለውም ማለት ነው ስለዚህም የፖለቲካ ሃሳቡን አስተካክሎ ዳግም እራሱን ብዙ ሽንኩርቶች ለማግኘት መዘጋጀት አለበት አልያም በምርጫ ቀኑም የሚጠብቀው ውጤት ከዚህ የራቀ ስለማይሆን ሽንፈቱን ከውዲሁ ያውቀዋል ማለት ነው።

ለዚህም ነው እያንዳንዱ የፖለቲካ ተወዳዳሪ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርግባቸው አካባቢዎች በርከት ያሉ የሽንኩርት እንዲሁም ሌሎች አትክልቶች እንዲበረከቱለት የሚያስችል ሃሳብና ማግባቢያ ይዞ በገበያዎች ውስጥ ሲንከላወስ የሚውለው ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደው የመካከለኛ ዘመን ምርጫ ታዲያ አስቀድመውም ተወካዮቻችውን በላኩባቸው አካባቢዎች ሁሉ በርከት ያለ የሽንኩርት ስጦታ ስላላገኙ ሲፈሩ የነበሩት የደሴቲቱ ፕሬዘዳንት ሳ ኢንግ ዊን የፈሩት አልቀረላቸውም ።

ፓርቲያቸውዲሞክራቲክ ፕሮግረስ በቂ መቀመጫ ሳያገኝ ቀርቷል። ዲሞክራሲ ባህል የሆነባት ታይዋን ፕሬዝዳንትም ድሮም የሽንኩርቱን መጠን ሳይ ውጤቱን ገምቻለሁ ያሉ ይመስላል ቅዳሜ ምርጫው ተከናውኖ እርሳቸው እሁድ ስልጣናቸውን አሽናፊው ፓርቲ ቢይዘው ይበጃል ብለው ስላጣናቸውን ለቀዋል።

እናም ስልጣኔን ከባህል ባጣመረችው ታይዋን የሽንኩርት ስጦታ የምርጫ ውጤትን ወሳኝ መሆኑን ዛሬም አስመስክሯል።

በማህሌት አማረ
2022-11-28