ይህ በቻይና የተለመደ አይደለም አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞን ማሰማት። እንዲህ በስፋት ሲታይ በዘምናዊቷ ቻይና የመጀመሪያ ነው ተብሎለታል።
የነገሩ መንስኤ የሀገሪቱ መንግስት በኮቪድ ሳቢያ የጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በዛ የሚል ነው።በምዕራብ ቻይና ኡርሚክ ከተማ በአንድ የመኖርያ አፓርትመንት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ህጻናትን ጨምሮ 10 ሰዎች የሚደርስላቸው አጥተው ህይወታቸው ማለፉ ደግሞ ዜጎች ህጉን ሁሉ ጥሰው አደባባይ እንዲውጡ አድርጓል ።
ተቃውሞው ከከተሞች ወደ ከተሞች መስፋፋቱ ሳያንስ የእንቅስቃሴ ገድቡ ይነሳልን ከሚለው በተጨማሪ የዢ ጂንፒንግ አስተዳደርም ይነሳልን አይነት ጥያቄ መያዙ ነገሩ እንዲከር አድርጎታል።
ፒንግ ደግሞ ከሁለት አመት በፊ መነሻውን በሀገሬ ያደርገው ኮቪድ ህዝቤን እንዳይጨርስ ማድረግ የቻልኩት ሌላው አለም ሚሊዮኖችን ሲያጣ እኔ በሺዎች የገደብኩት በእዚህ የእንቅስቃሴ ገደብን በሚጥለው ህግ ጥብቅ ትግበራ ነውና አቋሜን አልቀይርም ባይ ናቸው።
ለነገሩ ውስኔውን ጥቂት ለማላላት በተሞከረባቸው ግዛቶች በአንድ ቀን የመያዝ መጠን አዲስ ክብረ ወስን አስመዝግቦ 40 ሺ መድረሱ በውሳኔያቸው መጽናታቸው ተገቢ ነው ያስብላል የሚሉም አሉ።
ቻይናውያኑ ግን ገድቡ የበለጠ አደጋ ነው ሰልችቶናል በአካልም በመንፈስም እያደከምን ነው ብለው አደባባይ ወጥተዋል ።በተለይ እነዚያ የሚደርስላቸው አጥተው በእሳት አደጋ የሞቱት ዜጎች ሌላ ግዜ ቢሆን በቀላሉ የሚተርፉ መሆናቸው የእንቅስቃሴ ገደቡ ዋንኛ የምሬት ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ለጤናችን የተባለ ነገር ህይወታችንን ካጠፋ ምን ይፈይድልናል የሚል ነው ተቃውሞቸው። በአንዳንድ ግዛቶች የአካባቢ ባለስልጣናት ኮቪድን ለመከላከል ነው በሚል ምንነቱ የማይታወቅ መድሃኒት በግድ እያዋጡን ነው የሚሉ ድምጾች መስማታቸው ደግሞ ተቃውሞውን በጣም አባብሶታል።ወትሮም በሰብዐዊ መብት አያያዝ ለሚወቅሷት ምዕራባውያን ደግሞ ሌላ የክስ ምክንያት ሆኖላቸዋል።
አሁን የንቅስቃሴ ገድቡን የሚቃወምው ሰልፍ ከቻይና አልፎ ቻይናውያን ባሉበት የአውሮፓ ከተሞችና በሆንግ ኮንግ ተስፋፍቶ ቀጥሏል። በሀገር ቻይና ያሉ ዜጎቻችን ታፍነዋል ያሉት እኒህ ቻይናውያን ድምጽ እንሆንላቸዋለን ብለዋል።
ለእዚህም ነው የቻይና ኤንባሲዎች ባሉበት ሁሉ ተቃውሞቸውን እያሰሙ ያሉት። በየአምስት አመቱ በሚካሄድ የኮምኒስት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ከወራት በፊት የእድሜልክ መሪነታቸውን ላርጋግጡት ዢንፒንግ ይህ ያልተለምደ መንግስትን ተቃውሞ አደባባይ የመውጣት መንገድ ፍጹም ተቀባይነት ያለው አይደለም ።
ለዚህ ነው ፖሊስ ተቃውሞውን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ያዘዙት ። ይህ ግን ተቃውሞውን ከማርገብ ይልቅ መልኩን ቀይሮ ሰውዬ ከስልጣን እንዲወገዱ ወደ መጠየቅ አሳደገው እንጂ ያመጣው ለውጥ የለም ። እንደውም ተቃውሞው ከግዛት ግዛት እየተሸጋገረ ተጠናክሮ እንዲቅጥል አቅም ሆኖታል እየተባለ ነው።
ነገሩ በኮሚኒስቷ ቻይና የተለምደ ስላልሆን ትኩርትን ሳብ እንጂ የተጠናከር መዋቅር ያለው የዢን ፒንግ አስተዳደር ከቀናት በኋላ በአግባቡ ይቆጣጠረዋል የትም አይደርስም የሚሉ ብዙዎች ናቸው።
በብሩክ ያሬድ
2022-11-29
