እስካሁን ባለው የሰብል ስብሰባ ወቅት በ4ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት በቆላማ አካባቢዎች የሰብል መሰብሰብ ስራው እየተጠናቀቀ ነው ተብሏል።
በወይና ደጋ አካባቢም በብዛት እየተሰበሰበ ነው።በደጋ አካባቢዎች ግን ትንሽ ዘግየት ብሎ የሰብል ስብሰባ እንደሚጀመር የተወሰኑ ሰብሎች ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልበት ዕድል ስለሚኖርም የከተማው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች ሳይቀሩ ተረባርበው አርሶአደሩን በሰብል ስብሰባ ሊያግዙ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
በዘንድሮው የመኸር እርሻ በአጠቃላይ 13.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈናቸውን እና ከመኸር እርሻው በአጠቃላይ 400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተነግሯል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-11-29
