ሀገሬ ቲቪ

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሰላም ላይ ያተኮረ ውይይት ተጀመረ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላይ ያተኮረው ሦስተኛው ዙር ውይይት በኬኒያ ተጀመረ።

ውይይቱ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ያሉ ታጣቂ ኃይሎት ትጥቅ ስለሚፈቱበት ፣ ታጣቂዎቹ የተሀድሶ ስልጠና ስለሚያገኙበት እና መደበኛን የጦር ኃይል ስለሚቀላቀሉበት ሁኔታ መምከር ዋንኛ ዓላማው እንደኾነ የቀድሞ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ሰላም እንዲመጣ ቁርጠኛ መኾናቸውን በውይይቱ እየተሳተፉ የሚገኙት የኬኒያ፣ የቡርንዲ፣ የሩዋንዳ እና ዩጋንዳ መሪዎች ገልጸዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-11-29