ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል ክትባት መስጠት ጀመረች። በቅርቡ በሰሜን ምዕራብ ምባንዳካ ከተማ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አስታውቋል በዚሁ አካባቢ ከሁለት መቶ የሚልቀ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውም ተረጋግጧል ለዚህም የኢቦላ ህክምና ማዕከል በከተማዋ መዘጋጀቱ ተሰምቷል። በፈረንጆቹ 2020 በምባንዳካ ከተማ በኢቦላ መያዛቸው ከተረጋገጡ 130 ሰዎች ውስጥ 55 ሰዎችን ገድሏል። ኢቦላ በ1976 በማዕከላዊ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀው የቫይረስ ዓይነት መሆኑን ሲጂቲኤን አፍሪካ አስነብቧል።
በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28
