ሀገሬ ቲቪ

17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ

መረጃዎችን ለመጠበቅ ጠንካራ የሆነ የመረጃ ቋት ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። መረጃን ማስተዳደር የግለሰቦችን መብት የሚያከብር እና ኢኮኖሚን የሚያግዝ የተሳሰረ መሆን እንዳለበት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብር በንግግራቸው አንስተዋል።

ኢንተርኔትን ለሁሉም በማዳረስ ረገድ ኢትዮጵያ የሰራቻቸውን ስራዎች በስፋት ጠቁመዋል።

ጉባኤው የሳይበር ምህዳሩ ሀቀኝነት፣ ፍትሃዊነት እና ደህንነት ለመገንባት በሚያስችል መልኩ እንዲቃኝ ትኩረት ሰጥቶ ሊመክር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-11-29