የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ምርቶች ተመሳሳይ ደረጃን በመያዝ በቀላሉ ወደ ዓለም ገበያ እንዲቀላለቀሉ ማስቻልን አላማ አድርጎ የተነሳው የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት 67ኛ ጉባኤውን በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ እያካሔደ ነው።
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት በቀለ ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እያሳደገች ባለችበት በዚህ ሰዐት እንዲ አይነት ጉባኤዎችን ማኪያሄዷ ከምርቶች ጥራት ባለፈ አህጉራዊ ግንኙነቶችን እንደታጠናክር ይረዳታል ብለዋል።
ከ20 በላይ ከአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ጉባኤው ምርቶችን ወደ ዓለም ገበያ ለማምጣት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ለ 4 ቀናት እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
በዮሴፍ ከበደ
2022-11-29
