ሀገሬ ቲቪ

የሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ላለፉት በርካታ አመታት ምክክር ለብዙ ሃገራት ግጭቶችን ለመፍታት እና ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግርን እውን ለማደረግ ተተግብሯል።

ኢትዮጲያ በህዘቦች መካከል ያለን ልዩነት እና ግጭቶች በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት እየሰራች ትገኛለች ። ለዚህም ከ 9ወር በፊት የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሺን የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በአሁን ወቅት የውይይት ተግባራት ለማከወን እና አጀንዳዎችን ለመቀበል ፅህፈት ቤቶችን በክልል ፡ በዞን እና በወረዳወች ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ፡፡

ነገር ግን ኮሚሽኑ አሁንም የሰሜኑ ጦርነት እና በኮሚሽኑ ዙሪያ አንዳንድ ወገኖች የሚፈጥሩት ብዥታ ተደግዳሮት እንደሆንበት ይገለጻል። የሃገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ኮሚሺኑ በሃገሪቱ ከሚገኙ ከ 40 በላይ ከሚሆኑ ፖለቲካ ፓርቲዮች ጋር እየሰራ ይገኛል ።

በተለያዩ ሃገራት የተካሄዱ ምክክሮች በአብዛኛው ስኬታማ ያልነበሩ ሲሆን ለዚህም የገዥ መንግስት ጣልቃ ገበነቶች እና ውጭ ሃገራት ሚና ይጠቀሳል ።

ኮሚሽኑ የተሳካ ሃገራዊ ምክክር እንዲኖር እና የወጭ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር በተቻለው አቅም የሃገር ወስጥ ባለሞያዎችን እንደሚጠቀም ገልጾ ሌሎች እገዛዎች የሚያስፈልጉ ሆነው ሲገኙ ከውጭ ባለሞያዎች ጋር ለመሰራት ሰምምነት እንዳለው ተገልጿል ።

ተቋሙ በ2015 አጋማሽ የውይይት ተግባሩን ለመጀመር እየሰራም እንደሚገኝም አስታወቋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-29