ከዛሬ 148 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን 1884 ዓ.ም በተላበሱት መልካም ስበዕና እና ደግ ልብ አለም በክብር የሚዘርክራቸው ኢትዮጵያም ዛሬ ውብ ሆኖ የሚታየውን መንገድ ቸርችል ጉዳና ስትል በስማቸው የሰየመችላቸው ታላቁ ሰው ዊንስተን ቸርችል ተወለዱ።
ከንጉሳዊያን ቤተሰብ የተወለዱት ቸርችል መደበኛ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወታደራዊ ኮሎጅ በመግባት በማዕረግ ተመረቁ ።
ከውልደታቸው ጀምሮ እስከለተ ሞታቸው ድረስ ለሰው ልጆች ጠቃሚ ያሉትን መልካም ተግባራት ያከናውኑት ቸርችል አንድኛው የዓለም ጦርነት በተቀሰቀሰ ጊዜ የተቀናቃኞችን ክንድ ለማብረክረክ በጦር መሪነት አዋግተዋል ።
ሁለተኛው የአለም ጦርነት ሲነሳም እኚ ሰው የ ብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነብሩና የናዚ ጀርመንና የተባባሪዎቿን እኩይ አላማ ለመቀልበስ እልህ አስጨራሽ ትግል አድርገዋል። ከብዙ ፈተናዎችና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የሁለትኛው የዓለም ጦርነት ተቋጨ ።
ከጦርነቱ በኋላ በተደረገ ምርጫ የ ቸርችል ፓርቲ ተሸነፈ ። እሳቸውም ተቃዋሚና ለሀገር እና ለህዝቦች ይበጃል ያሉትን ሀሳቦች በመዘንዘር ኑሯቸውን ቀጠሉ ።
ከ 6 ዓመት በኋላ በድጋሜ በተደረገ ምርጫ ቸርችል ድጋሜ በመመረጥ ጠቅላይ ሚኒስተር ለመሆን በቁ። በአንደኛውና በሁለትኛው የዓለም ጦርነት ብሎም ስልጣን በለቀቁበት ወቅት ለሀገራቸው የቆሙባቸውን ቀናት በማሰብ ህዝባቸው ዳግም ክብር ሰጣቸው ።
ከፖለቲካዊ ህይወታቸው ባሻገር ድንቅ ሀሳቦችን በመጽሀፋቸው በመከተብ ለአንባቢያን ማድረሳቸው በዓለም ዙሪያ የሚወደዱበት ሌላኛው ገጽታቸው ነው ።
ተሳታፊ የነበሩበትን ሁለተኛው የዐለም ጦርነት ጽፈው ለአንድባቢያን አድርሰዋል ። በመጸሀፎቻቸውም የኖቤል የስነጽሁፍ ሽልማት የተበረከተላቸው ብቸኛው ብሪታኒያዊ ሆነዋል ።
እኚ ሰው በሚያሳዩት መልካም ስብዕና እና በተላበሱት ደግ ልብ ከሀገራቸው አልፈው ዓለም በክብር የምትመለከታቸው ተጽኖ ፈጣሪ ሰው ናቸው።
አሜሪካን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራትም የክብር ዜግነት ተሰጥቷቸዋል ። በዛሬዋ ዕለት በ1884 የተወለዱት ዊኒስተን ቸርችል በ91 ዓመታቸው ጥር 24 ቀን 1965 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-11-30
