ሀገሬ ቲቪ

ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት አጋር አካላት 148.7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት እየሰጡ ላሉ አጋር አካላት የ148.7 ሚሊዮን ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።

የአጋር አካላቱ 16 ሲሆኑ ድጋፉ የተደረገላቸው በክልሉ እየሰጡ ላሉት የሰብዓዊ አቅርቦት መሆኑን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በትግራይ ውስጥ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ከ45 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲሁም 839 ሜትሪክ ቶን በላይ መድሃኒት መሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደበበ ወደ ክልሉ የሚደረገው ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-11-30