የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ እንዳሉት መንግስት በትግራይ ክልል ኢንተርኔትን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ የለም።
ሚንስትሩ አገልግሎቱ ከመብራት እና ስልክ አገልግሎቶች መጀመር ጋር አብሮ የሚከወን መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ዓመታዊ የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ላይ ነው።
ነገር ግን መንግስት አገልግሎቶቹን ለማስጀመር መርሀግብር እያዘጋጀ መሆኑን መናገራቸውን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ አስነብቧል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-11-30
