ሀገሬ ቲቪ

በሶሪያ ጉዳይ ተርኪዪ እና ኢራን ተወያዩ

ኢራን እና ተርኪዪ በተርኪየ እና ሶሪያ ድንበር እያደገ ባለው ውጥረት ላይ ተወያዩ። የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሴን አሚር አብዶላህያን እና የቱርኩ አቻቸው በድንበሩ ስላለው ወታደራዊ ውጥረት በስልክ ተነጋግረዋል።

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የድንበር ችግሮቹን ወታደራዊ ርምጃዎች ያወሳስቧቸዋል ከዚያ ይልቅ ለውይየት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከሶርያ ጋር የተገባው ውጥረት በውይይት ለመፍታት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

ቱርክ በሶርያ ይሉ ከኩርዲስታናውያን ለደህንነቴ ስጋት ናቸው በሚል የሚሳየል ጥቃት መጀመሯ ከሶሪያ ጋር ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

አሁን ኢራን በአሸማጋይነት መግባት ጉዳዩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ይረዳል ተብሏል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-30