ሀገሬ ቲቪ

የሩሲያ ዛቻ ለምዕራብአውያን

ፕሬዝዳንት ቭላድሚርፑቲን በዩክሬን ጉዳይ እጁን የሚያስገባ የምዕራብ ሀገር ላይ መብረቃዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ አሜሪካ ለዩክሬን የጦር ድጋፍ ማድረግ ይቅርብሽ ሲሉ ፑቲን አስጠንቅቀዋል። የምዕራቡ ሀገራትም ለዩክሬን እያደረጉት ያለው የጦር ድጋፍ እሳት ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፑቲን ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ ተለያዩ ክፍሎች ለመከፋፈል ይፈልጋሉ ብለዋል ዳር ሆኖ በጉዳያችን አስተያየት የሚሰጥም ሆነ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክር ካለ መብረቃዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ፑቲን ዝተዋል። ለዚህ ደግሞ ካስፈለገ የትም ሀገር የሌለውን የጦር መሳሪያችንን መጠቀም እንችላለን ሲሉ ተደምጠዋል የአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን በበኩላቸው ዛሬ ዩክሬንን መርዳት ስለሚቻልበት ሁኔታ እንደሚመክሩ ነው የተገለጸው።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28