ሀገሬ ቲቪ

የብሪታኒያ እና የቻይና ግንኙነት

ዘለግ ያለ አመታትን ጥሩ የተባለ የኢኮኖሚ ግንኙነት ያላቸው ናቸው ብሪታኒያ እና ቻይና። ይህ የጠነከረ የኢኮኖሚ ወዳጅነት ደግሞ ብሪታንያ በሌሎች ሀገራት ላይ በዋናነት የምታነሳው የስብዐዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ችላ እንዲባል አስችሎታል የአዲሱ ጠቅላይ ሚንስተር ሪሺ ሱናክ ሀሳብ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለመጀመርያ ጊዜ የውጭ ፖሊሲያቸውን አስመልክቶ ባደርጉት ንግግር ሀገራቸው በቻይናም ላይ ቢሆን ከስብአዊ መብት አያያዝ ታሳየው የነበረው የተለሳለሰ አቋም አሁን አይቀጥልም ብለዋል።

ብሪታኒያ በእሳቸው ዘመን ጠንካር ያለ አመላከከት በሰብዕዊነት ላይ መያዝ ትጀምራለች ።ይህ ማለት ግን አሁንም የቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ያላትን ድርሻ እንዘነጋለን ማለት አይደለም ብለዋል።

እንደአየር ጸባይ ለውጥ ባሉ አለም አቀፍ ጉድዮች ላይ አብረን አንሰራም ማለት አይደለም ብለዋል። ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱ ያቀራረብ መንገዱን ይቀይር ይሆናል እንጂ ችላ አይባልም ሲሉ ነው የተናገሩት።

ቻይና በሃገሯ በኮቪድ ሳቢያ የተጣለን የእንቅስሴ ገደብ ተቃውመው በወጡ ዜጎቿ ላይ የሃይል እርምጃን መውሰዷና በዚህ ወቅት ለሁነት ሸፋን ሲሰጥ የነበረን አንድ የቢቢሲን ጋዜጠኛ በቻይን ፖሊሶች መያዙ ደግሞ ለጠቅላይ ሚንስትሩ መረር ያለ አቋም መንሳኤ እንደሆነ ተነግሯል ።

ወትሮም በሰብአዊ ጉዳይ አያያዝ እና በታይዋን ጉዳይ ትችቷን ለምትሰነዝረው ብሪታኒያ ይህ ትልቅ ምክንያት ነው።

“የቻይና መንገስት የዜጎችን ተቃወሞ ለማፈን የሚደርገወን ጥረት እንቃወማለን ፣ በቢቢሲ ጋዜጠኛ ላይ የደርሰውን ተመለከተናል ። መንግስታችን ሚዲያዎች በነጻነት እንዲስሩ ያምናል ። በዢንግ ዣንግ እና በሊሎች አከባቢዎች የሚደርጉ ተቃወሞች በነጻነት ይደርጉ ማንም ጣልቃ ሊገባበት አስይፈልግም።”

ብሪታኒያ ከቻይና ጋር ያልትን ግንኙነት አላልታ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ እና ከጃፓን ጋር ያላትን በዲፕሎማሲ ይበልጥ ወደ ላቀ ደርጃ ማሳደግ ፍላጎታቸው እንደሆነ ሪሺ ሱናክ ተናግረዋል ።

ሃገራቱ እንዲ አይነት የቃላት ሽኩቻ ውስጥ ይግቡ እንጂ በዘንድሮ አመት ብቻ ከ 92.9 ቢልየን ፖውንድ በላይ የንግድ ለውውጥ አደርገዋል ።

በቱሪዝም ዘርፉ ውስጥም ቢሆን ሁለቱ ሃገራት በዚ አመት በቻ ከ 1.1 ቢልየን ፓውንድ በላይ ገቢን ተጋርተዋል ።

የብሪታኒያው መሪ ይህን ማለታቸውን ተከትሎ በወሳኔያቸው ያልተደስቱ የካቢኔው አባላት ቻይና የብሪታኒያ አራተኛ የንግድ አጋር በሆነችበት በዚህ ወቅት ይህ ውሳኔ ያልተጠና እና ድጋሚ ሊታስበበት የሚገባ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተችተዋል ።

አካሄዱ ቻይናን እንደስጋት ያየ ነው ይህ ደግሞ ፍጹም የተሳሳተ ነው ሲሉ ሞግተዋቸዋል። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቻይና ላይ ስንከተለው የነበረ ለኢኮኖሚ ሲባል ሰብአዊነትን ቸል የማለት መንገድ ከዚህ በኋላ አብቅቶለታል እያሉ ነው።

ውሳኔያቸውን ባሰቡት ልክ ተግብረውታል ወይ የሚለው ግዜ የሚፈታው ጉዳይ ቢሆንም።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-11-30