ሀገሬ ቲቪ

የዓለም የኤች አይቪኤድስ ቀን

በዓለማችን ከተከተሱ ወረርሺኞች የሰው እርን ያለርህራሄ ቀትፏል። ወደ 48.6 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ለሞት ተዳርገዋል። HIV AIDS በተመራማሪዎች የተሰጠው ስያሜ ነው።

ቫረሱ የሰዎችን በሽታ የሚከላከል ሴልን በመጨረስ ለሌሎች ህመሞች አሳልፎ የሚሰጥ እና ኋላም ለሞች የሚዳርግ ነው።

ቫይረሱ ተከሰተ በተባለበት አራት ዓመታት ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚልቁ ሰዎችን መያዙን መረጃዎች ያመለክታሉ።

1981 ዓ.ም. ታዲያ የዓለም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለመጀመሪያ ግዜ ቫይረሱን ለመዋጋት የዛሬዋን ቀን ቫይረሱን ለመከላከል ይታሰብበት ዘንድ መርጦታል።

ቀኑ በዓለማችን ላይ ጤናን በተመለከተ ይከበር ዘንድ ከተሰየሙ ዘንድ የመጀመሪያው ነው። ታዲያ ቫይረሱ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ 113 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

ዛሬ ላይ 38 - 43.8 ሚሊዮን የሚሆነው የእዓለማችን ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። ከእነዚህም ውስጥ 2.1 ሚሊዮኖቹ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ናቸው።

አሁን የተረሳ እስኪመስል ድረስ በሽታው ላይ ያለው መዘናጋት በርካቶችን እየገበረ ይገኛል። በባለፈው የፈረንጆቹ ዓመትብቻ 2 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃዎች ይጠቁምሟል። 5.9 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ይህችን ዓለም ተሰናብተዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያም ቢሆን 12 ሺሕ ሰው በየዓመቱ በቫይረሱ እንደሚያዝ የጤና ሚንስቴር መረጃ ያመላክታል። ከዚህም ውስጥ 69 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ ይገልፃል።

ይህ ቁጥር በጤና መስጫ ተቋማት ሄዶ ምርመራ ካደረጉ ሰዎች የተገኙ ሲሆኑ የቫይረሱ ምርመራዎች በስፋት ቢደረጉ ቁትሩ ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል።

ታዲያ መዘናጋቶች የሸበቡት ይህ ቫይረስ ለሁሉም ፍትሀዊ የሆነ የቫይረሱ ምርመራ እና መረጃዎች ተደራሽሽነት ላይ መሰረት ተማድረግ ይከበራል።

በሀገራችንም እንዲሁ በስፋት እንደሚከበር የጤና ሚንስቴር አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታትም በ2023 ዓ.ም. ይህንን ቫይረስ እስከነአካቴው ለማቆም እቅድን ይዟል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-01