ሀገሬ ቲቪ

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በኦላይን ለመስጠት ዝግጅ መጀመሩ ተገልጸ

ትምህርት ሚንስቴር የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

በኦንላይን የሚሰጠው የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች በተጨማሪ የማታና የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና በግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ሚኒስትር ዴኤታ ጠቁመዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ለፈተናው የሚያግዛቸውን መሰረተ ልማቶች በሟሟላት ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚንስትር ዴኤታው አሳስበዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-01