ሀገሬ ቲቪ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዝቅተኛ ኑሮ ላለው ማህበረሰብ ይሆናል ያሉትን ፈንድ ይፋ አደረጉ

ዊሊያም ሩቶ ያስተዋወቁት ፈንድ ለድሃው ማህበረሰብ የብድር አገልግሎት የሚውል ሲሆን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሽቆልቆል ይታደጋልም ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ይሄንን ፈንድ ለድሃው ማህበረሰብ እንደሚያመቻቹ ቃል ገብተው ነበር። በዚሁ ፕሮግራም አንድ ሰው 50 ሺህ የኬንያ ሺልንግ ያክል በስልክ የገንዘብ ማስተላለፊያ አፕሊኬሽን መበደር እንደሚችልም ተገልጿል።

ለዝቅተኛው ማህበረሰብ የብድር አገልግሎት የሚሰጠው 407 ሚሊዮን ዶላር ወይም 50 ቢሊዮን ሺሊንግ በጀት የተያዘለት ፈንዱ ከአምስት ዓመት በላይ እንደሚቆይ ተገልጿል።

በአብርሃም በለጠ
2022-12-01