ሀገሬ ቲቪ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፉሳ ከሙስና ጋር በተያያዘ ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል ተባለ

ሾልኮ በወጣ አንድ ሪፖርት ራማፎዛ ስልጣናቸውን ያለ አግባባ መጠቀማቸውን እንዲሁም የጸረ ሙስና ህጉን መጣሳቸውን ያመልካታል ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በግል የእርሻ መሬታቸው የተደበቀ ሕገ ወጥ 4 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ ተሰምቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ለዋሉ ግለሰቦች ጉቦ በመስጠት ጉዳዩን በዝምታ እንዲታለፍ ጥረት አድርገዋል በሚል ነው የተጠረጠሩት ።

ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ይህን ድርጊት አልፈጸምኩም ብለዋል ። በጉዳዩ ላይ የሃገሪቱ ፓርላማ በሚቀጥለው ሳምንት ጉዳዩን መርምሮ ራማፎሳ ላይ ክስ የመመሰረቱ ሂደት ይጀመር ወይም አይጀመር የሚለውን ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-01