ሀገሬ ቲቪ

አስገራሚው የየግመሎች የቁንጅና ውድድር በኳታር

ዓለምን ያስገረመ አዳዲስ እና ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያስተናገደች የምትገኘው የአለም ዋንጫ አዘጋጇ ሃገር ኳታር አሁንም በሌላ የውድድር መስክ ዓለምን አጀብ እያሰኘች ነው።

ይህ ውድድር የቁንጅናውድድር ነው፡፡ የቁንጅና ውድደር ምኑ ያስገርማል ታዲያ ትሉይኾናል! አስገራሚው እና እንዲህም አለ ወይ ያስባለው ውድድሩ የሰዎች ሳይኾን የግመሎች መኾኑ ነው። በረሃማዋ ኳታር ለምን በሰው ልጆች ብቻ የቁንጅና ውድድር ይወሰናል የበርሃ መርከበኞቻችን በቁንጅንና ውድድር መሳተፍ ይችላሉ ብላለች፡፡

በዚህ የግመሎች የቁንጅና ውድድርም ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ እና መወዳደር እንፈልጋለን ያሉ ግመሎች በባለቤቶቻቸው እየተመሩ የቁንጅና ውድድሩ ላይ ተሳታፊ ኾነዋል።ውድድሩ እንዲሁ ለይስሙላ የተደረገ አይደለም ይለናል የቢቢሲ ዘገባ።

ይልቁንም ተወዳዳሪ ገመሎች የተለያዩ ምርመራዎች እና ፈተናዎችን ማለፍ ግድ ይላቸዋል። የውድድሩ አዘጋጆች ለቁንጅና ውድድሩ ተመርጠው የሚመጡ ግመሎችን ምንም አይነት መጭበርበር እናዳይኖር ጥብቅ ምርመራ ያደርጋሉ።

እንዴት ካላችሁ! የግመሎቹ ባለቤቶች ለቁንጅና ውድድር ያሰለፏቸውን ግመሎቻቸው አምረው እና ተፈጥሮአዊ ውበታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያደርጉ መድኃቶችን የዘረ-መል ሕክምና አለማድረጋቸውን በኤክስሬይ መመረመሪያ ማሽን ይጣራል።ከዚያ ነው ለውድድሩ ብቁ መኾን የሚችሉት።

ይሄን ሁሉ ካለፉ በኋላ ታዲያ ለውድድር ብቁ ናቸው የተባሉት ግመሎች በእድሜያቸው እና ባላቸው ዝርያ ተከፋፍለው ለውድድሩ ይቀርባሉ።

በውድድሩ ላይም የሚታለቡት የወተት መጥን ለአሽናፊነት ከሚያበቋቸው መስፈረቶች መካከል ዋነኛው ነው። በውድድሩ አሸናፊ የሆነች አንዲት ግመልል ታዲያ በአንግቷ ላይ የሚታሰር ስጦታ ይበረከትላታል። ለግመሏ ባለቤትም ታዲያ ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት ይበረከትለታል።

ይህ ውድድር ሲካሄድ ያሁኑ የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ በፊት የተካሄዱ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ ግመሎች ለየት ያለ ክብር የሚሰጣቸው ሲሆን ባለቤቶቻቸውም እስክ ሁለ መቶ ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ነበሩ።

በማህሌት አማረ
2022-12-01