ሀገሬ ቲቪ

ዩክሬን ምን ያህል ወታደሮቿን አጥታለች?

282 ቀናትን የተሻገረው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት በርካታ ክስተቶችን እያስተናገደ ቀጥሏል በዚህ ጦርነት ግን ብዙም ጠንከር ብሎ ሳይሰማ የቆየ ጉዳይ ቢኖር ሁለቱ ሀገራት ምን ያህል ወታደሮቻቸውን በጦርነቱ አጡ የሚለው ይጠቀሳል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ የኾኑት ሚካይሎ ፖዶልያክ ዩክሬን ከ 10 ሺህ እስከ 13 ሺህ የሚገመቱ ወታደሮቿን አትታለች ሲሉ በይፋ መናገራቸውን በርካታ ብዙኃን መገናኛዎች የፊት ገጻቸው ላይ አስፍረውታል።

የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት በዝምታ የሸፈኑትን ጉዳይ አማካሪው መናገራቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

የቮለድሚር ዘለንስኪ አማካሪ ቀጥለውም በሰኔ ወር በየቀኑ ከ 100 እስከ 200 ወታደሮቻችን ማጣት የለመድነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሚካይሎ ፖዶልያክ ግን የተናገርኩት ቁጥር የጦር ኃላፊዎችም የሚያውቁት መዝግበው ያስቀመጡት ነው ማለታቸውን ደግሞ አልጀዚራ አስነብቧል።

ዘገባው አክሎም የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ጊዜው ሲደርስ ሁሉንም ነገር ያብራራሉ ማለታቸውን ገልጿል።

የዩክሬን መከላከያ ኃይል ሚካይሎ ፖዶልያክ በተናገሩት ላይ ምንም ዓይነት ሀሳብ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዐት አልሰጠም።

አማካሪው በጦርነቱ ስለተገድሉ የሩሲያ ወታደሮች ሲያወሩ፤ ሩሲያ ወረራውን ከጀመረች አንስቶ 100 ሺህ ወታደሮቿን በጦርነቱ ገብራለች 150 ሺህ ወታደሮቿ ደግሞ ቁስለኛ ኾነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሩሲያ ግን በጉዳዩ መልስ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን የመረጠች ይመስላል። ቢቢሲ ግን ሩሲያ እስካሁን ያጣቻቸው ወታደሮች ከ9300 በላይ ነው 100 ሺ አይደርስም እርግጠኛ መረጃ ነው ሲል ይፋ አድርጓል። ይህ የሞት ቁጥር ጨምራል እንኳን ቢባል ከ 18600 እንደማያልፍ ነው በዘገባ የጠቆመው።

ባለፈው ወር ዩክሬንም ሩሲያም ሁለቱም እያንዳንዳቸው 100 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮቻቸው ሙት እና ቁስለኛ ኾነዋል ሲሉ ማርክ ሚሌይ የተባሉት የአሜሪካ የጦር ጀናር መናገራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-02