አይደለም አይተዋት ስሟንም ሲሰሙ የሚፀየፏት በርካቶች ናቸው። ታዲያ በእየጓዳችን መከራችን የሚያበሉን እነዚሁ ቀበኞቹ አይጦች ከወደ አሜሪካ ለኒውዮርክ ፈተና ሆነዋል መባሉን ሰማን እና ልናጋራችሁ ወደድን።
አይጦቹ ታላቋን ከተማ ኒውዮርክን የአይጦች ከተማ አሰኝቷታል። ታዲያ በዚሁ የተማረሩት የከተማዋ ባለስልጣናት አደገኛ የአይጥ አዳኝ ለመቅጠር መከራቸውን እያዩ ይገኛሉ።
በከተማዋ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡት እና ነዋሪዎቿን መከራ ውስጥ የከተቱትን አይጦች ለመከላከል የሚረዳ ቢሮ ማቋቋማቸውን የከተማዋ ከንቲባ ተናግረዋል።
ይህንን ቢሮ ለሚመራው ደመመራራ ደግሞ ከ120 እስከ 170 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር እከፍለዋለሁም ብለዋል።
ታዲያ በዚህ ቢሮ ውስጥ ለመቀጠር ቆፍጠን ያለ ወኔ እና ልበደንዳና መሆን መስፈርቱ ነው ሲል ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት አስነብቧል።
እነዚህ አይጦች በተለይ በከተማዋ ባሉት የባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ለተሳፋሪዎች ፈተና ናቸው። በባቡር ጣቢያው ውስጥ ወዲህ ወዲያ ሲመላለሱ ማየት አዲስ አይደለም።
በከተማዋ ወደ 9 ሚሊዮን የሚገመቱ አይጦች በከተማዋ መኖራቸው ይገመታል። ይህን ቁጥር የከተማዋ ባለስልጣናት በጥናት የተደገፈ አይደለም ሲሉ አይስማሙበትም።
የከተማ ነዋሪዎች እነዚህ ቀበኞቻችን ቁጥራቸው ከዚያም ሳይበልጡ አይቀሩም ባይ ናቸው።
ከጓዳ ዎቻቸው እስከ መዝናኛ ስፍራዎቻቸው፤ በመጓጓዣዎቻቸው ውስጥም ቢሆን ያለ ክልካይ እንዳሻቸው ይሆናሉ።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-02
