የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለን ጨምሮ በሙስና ወይም ሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ብሔራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴው ወደ ስራ መግባቱን እና እየወሰዳቸው ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰትቷል።
ኮሚቴው ሶስት ንዑስ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ የመንግስት አግልሎት አሰጣጥ፣ ፋይናንስና ግዥ፣ በፍትህ ስርዓቱ እና በመሬት አስተዳደር እንዲሁም በመሰረታዊ ፍጆታ አቅርቦት ዘርፎች ላይ ሙስና ወይም ሌብነት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚስተዋልባቸው በመለየት በሙስና ወንጅል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።
በማህሌት አማረ
2022-12-02
