ሀገሬ ቲቪ

የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ደህንነት እየተፈተሸ ነው

የግድቦች ደህንነት ፍተሻ እየተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። ተቋሙ ኃይል ማመንጫ ግድቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ እሰራሁ ነውም ብሏል።

ፍተሻው ግድቦች ሲሰሩ ጀምሮ ወደ ስራ ከገቡም በኋላ በግድቡ ላይ የውሃ መጠን ሲጨምር እና ሲቀንስ እንዲሁም የግድቡን ደህንነት ስጋት ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ያልተጠበቁ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ክስተቶችን ለመከታተል እንደሚረዳ ተገልጿል።

መረጃውን ከተቋሙ ድረ ገፅ አግኝተነዋል።

በማህሌት አማረ
2022-12-02