
ኦሚክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ እንደአዲስ ማገርሸቱን የቦትስዋና መንግስት ይፋ አድርጓል።
በቦትስዋና የተከሰተው ይሄው ኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ በሌሎች የአውሮፓ እና የኤዥያ ሃገራት የተስተዋሉ ናቸው ሲል የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል።
እስከ ዛሬ በተመዘገበ መረጃ 326,633 ሺሕ ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸውን ይፋ አድርጋለች። 2,790 የሚሆኑትን ደግሞ በሞት ተነጥቃለች።
የአለም የጤና ድርጅትም ይሄው አዲሱ ኦማይክሮን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ በመላው አለም በፍጥነት እየተሰራጨ ይገኛል ማለቱን ሲቲጂኤን አፍሪካ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2022-12-02