
ሩዋንዳ ወታደሮቿ በሞዛምቢክ በካዶ ዴልጋዶ የሰላም ማስከበር ዘመቻ በመሳተፋቸው የአውሮፓ ህብረት 20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።
የሀገሪቱ የወጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቪንሰንት ቡሩታ ከህብረቱ የተደረገላቸውን ድጋፍ ሲቀበሉ ሩዋንዳ በአህጉሪቱ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ቁርጠኛ ናት ብለዋል።
ሩዋንዳ ከነሐሴ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሞዛምቢክ ጥያቄ ወታደሮቿን እንዲሁም የፖሊስ ኃይሏን ወደ ካዶ ዴልጋዶ የሰላም ማስከበር ዘመቻ ልካለች።
ሩዋንዳ ወታደሮቿ ዛሬም ድረስ ሰላም ለማስከበር በሞዛምቢክ ናቸው ሲል ኢስት አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
በማህሌት አማረ
2022-12-02