ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ እና ፈረንሳይ አሜሪካ በምታደርጋቸው ድጎማዎች ዙሪያ ተወያዩ

አሜሪካ የዋጋግ ግሽበትን ለመካላከል በአሜሪካ አምራች ኢንደስተሪዎች፣ ለታዳሽ ሃይልን ማስፋፊያ ፐሮጅምቶችን የምታደርጋቸው የኢኮኖሚ ድጋፎች በአውሮፓ ያሉ ሌሎች አምራች ኩባኛዎችን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በሚያስችል መልኩ እንድታደርግ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን በአሜሪካ በነበረራቸው ጉብኝት ከባይድን ጋር መነጋገራቸው ተሰምቷል።

አለምን እያሰጨነቀ ያለው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እና የዋጋ ግሽበት አፍሪካን ክፉኛ ቢጎዳትም አውሮፓዊያኑ ላይም መጠንከሩ አልቀርም።

በተለይ ደግሞ የሩሲያ እና የዩኩሬን ጦርነት በአውሮፓ ያሉ አምራች ኩባንያዎች ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ከማድረጉም በተጨማሪ የሚያመርቷቸው ምርቶች ሰፊ ገበያ እያጡ መምጣታቸው የሰራተኞችን ቁጥር እንዲቀንሱ አስገድዷቸዋል። የኢኮኖሚ ቀውሱ የስራ አጥ ቁጥርን በአውሮፓ በፍጥነት እንዲጨምር አድርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዲያ አሜሪካ ክፉኛ በተጎዳው የአውሮፓ ኢኮኖሚ ላይ የራስ ምታት የሚሆን ውሳኔ አሳልፋለች። በአሜሪካ ለሚገኙ ኢንደስተሪዎች 430 ቢሊየን ዶላር ድጎማ አድርጋለሁ የሚል።

ይህ ደግሞ በጦርነት፣ በሃይል እጥረት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በዋጋ ንረት እየታመሰ ላለው አውሮፓ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነበታል። ምክኒያቱ ደግሞ አሜሪካ ለራሷ ኢንደስትሪዎች ከፍተኛ የሆነ ድጎማ ስታደረግ በአውሮፓ የሚገኙ ኢንደስትሪዎች የማምረት አቅማቸውና ያለው ዪኮኖም አለመረጋጋት በገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አያደርጋቸውም።

በዚህም አያበቃም በአለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ሲሉ በስራቸው ተቀጥረው የሚሰሩ እና ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰራተኞቻቸውን በወጪ ቅነሳ ሰበብ ስራ አጥ ያደርጓቸዋል ይህ ደግሞ ትልቅ ኪሳራን ያስከተላል።

የአውሮፓ መንግስታት ኢኮኖሚያቸው እየተዳክመ ስልለሆነ ለአምራች ኢንደስተሪዎችም ድጎማ ለማድረግ አቅማቸው አይፈቅድም። ለመንግስታቱም ቢሆን የአሜሪካ ድጎማ የማይወጡት የቤት ሰራ ሆኖባቸዋል።

ለዚህም ነው የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን በአሜሪካን ለሰራ ጉብኝት ባቀኑበት ወቅት በጉዳዩ ዙሪያ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር አሜሪካ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ብላ ለአሜሪካን አምራች ኢንደስተሪዎች፣ ለሃይል ማስፋፊያ ስራዎች የምታደርጋቸው ከፍተኛ ድጎማዎች አውሮፓዊያንን ያገናዘበ እንዲሆን እና ተመልሰው ያወጧቸውን የኢኮኖሚ ድጎማዎች እንዲያሻሽሉ እና ማስተካከያ በሚደረግበት ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው የተወያዩት ።

ማክሮን ከሲቢኤስ ስልሳ ደቂቃ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሜሪካ ያደረገችው ድጎማ አውሮፓዊያንን ያላገናዘበ መሆኑን ገልጸዋል።

ከባይደን ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ይሄንን አውሮፓዊያንን ያላገናዘበ የድጎማ ስርዓት በሚያስተካክሉበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል ማለታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል። ውይይቱን መሰረት አድርጋ አሜሪካ መች የድጎማ አካሄዷ ላይ ማስተካከያ እንደምታደርግ ግን የተባለ ነገር የለም።

በማህሌት አማረ
2022-12-05