ሀገሬ ቲቪ

የጽናት ተምሳሌት ኔልሰን ማንዴላ ያረፉበት ቀን

በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ ሰርአት ታግለዋል፤ ለ27 አመታትም በአንድ ጠባብ እስር ቤት ወስጥ የታሰሩ ሰው ናቸው፤ ኔልሰን ማንዴላ ። ዓለም ፊቱን ባዞረባቸው ወቅት ኢትዮጲያ ተቀብላ ወታደራዊ ስልጠናንም ሰጥታቸዋለች ።

ደቡብ አፍሪካ ነጻ ከወጣች በኋላ በፕሬዘዳንትነት ካገለገሉ በኋላ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በዛሬው ቀን ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ። የዛሬው እለቱን ከታሪክ ትኩረታችን ነው።

ዘረኝ ነትን ኩፉኛ ታግለዋል ፣ ፍቅርን ለአለም አስተምረዋል ፣ ይቅርታን ለከሳሾቻቸው አሳይተዋል ። አለም በነጻነት አባትነታቸው ያወቃቸዋል ደቡቡ አፍሪካዊ መሪ ኔልሶን ማንዴላን ። በዙዎች ማዲባም ይሏቸዋል ። ፕሬዘዳንቱ የተወለዱት በ 1910 ዐ.ም በደቡብ አፍሪካ ማቪዞ በተባለች መንደር ወስጥ ነው ።

የወደፊቱ የታያቸው የማንዴላ አባት ልጃቸው እንደ ተወለደ ሰሙን ሮ ሃላ ሃላ ማለት ሰም እንዳወጡላቸው ይነገራል ። ሰሙም በጦሳ ጎሳ ትርጓሜው ቅርንጫፎችን የሚሰብረ ፣ አሸናፊ ፣ ተጋጥሚዎችን የሚያናድድ ማለት ነው ።

ማንዴላ ኩፉኛ የዘረ መድሎ እና የነጮች የበላይነት የነገሰበትን የደቡብ አፍሪካ የፖሊትካን በወጣተነታቸው ተቀላቀሉ። በ1935 በደቡቡ አፍሪካ የሚገኘውን አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ተቀላቀሉ። ማንዴላ በናሽናል ኮንግረስ ፓርቲን በተቀላቀሉ ከ 4 አመታ በኋላ የነጭ አክራሪ ፓርቲ የደቡቡ አፍሪካን የስልጣን መንበር ተቆናጠጠ ።

ይህም ክስተተ በደቡብ አፍሪካ ህዘባዊ ተቃወሞ እንዲበረታ፣ እና ሰርአት አለበኝነቱም እንዲባባስ አደረገው ።ማንዴላም የተቀጣጠለውን ሀዝባዊ ተቃወሞ በመደገፈ በፓርቲወ አማካኘነት ተግሉን አቀጣጠሉት ።

በ1948 ዐ.ም ማንዴላ እና ሌሎች መቶ ሰዎች የአፓርትይድ ሰርአተን በመቃወም እስር ቤት ገቡ ። ከጥቂት ግዜያት በኋላ ከ እሰር የተፈተቱት ማንዴላ በ1953 ዐ.ም ከናሽናል ኮንገርሰ ፓርቲ ለቀቁ ።

ማንዴላ በመቀጠልም ህዝባ አስተባባረው በነጮች ላይ የተንጠለጠለውን ሰርአት ለመገርሰስ የሽምቅ ወጊያን ጀመሩ ። ለህዝባዊ ተቃወሞ እና የሽምቅ ወጊያወን ለማገዝም የተለያዩ ሃገራትን ድጋፍ ጠይቁ ።

በዚህ አጋጣሚ ታዲያ አለም አሸባሪ እና ነውጠኛ ነህ በሎ ያገለለውን ደቡብ አፍሪካዊውን ወጣት የወቅቱ ነጻ ሃገር ኢትዮጵያ ተቀበለችው።ታኅሣሥ አጋማሽ 1954 ዓ.ም ግርማዊ ቀዳምዊ አጼ ሃይለሰላሴ አቀባባበል አደርጉለት ።

ንጉሱ ለማንዴላ የጦርነት ትምሀርትም እንዲማር ፈቀዱለት ፣ ለማረፊያም እንዲሆነው በአዲስ አበበ ከተማ በሚገኘው ኮልፌ ፖሊስ ካምፕ ወስጥ ቤት ከነ ጠባቂዎቹ ሰጡት። ማንዴላ በኢትዮጲያ የቆየው ሶስት ወር ከ አንድ ሳምንት ቢሆንም ኢትዮጲያ ለማንዴላ ኢዮጲያዊ ዜነትን ሰጥታዋለች ።

ማንዴላ በኢትዮጵያ ፓስፖርት አውሮፓን ጨምሮ ወደ 15 ሀገራት ተጓዙውበታል። ማንዴላ በየ ሃገራቱ ያደረገወን ጉዞ አጠናቀው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመለሱ ግን ብዙም ሳይቆዩ በደህንነት ሃይሎች ተይዘው ለእስር ተዳረጉ ።

ማንዴላ የተከሰሱበትም ክስ የደቡብ አፍሪካን መንግስት በሃይል ለመናድ ሞክረውዋል እንዲሁም በሃሰትኛ የመንገድ ሰነድን ተጠቀመዋል በሚል ለ27 አመታቱ በሩበን ደሴት እስራት ተዳረጉ።

ከ27 አመታት በኋላ ከእስር የተፈቱት ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዝደንት በመሆን ተመረጡ ።በሃገሪቱ የትምህርት ፣ የጤና ፣ የኢኮኖሚ ለውጦች እንዲመጡ እና ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊያን የኑሮ ደረጃቸው እንዲሻሻልም ሰርተዋል ።

ማንዴላም ከዚህ በተጨማሪ በዘረኝት የተተበተወን የደቡብ አፍሪካን ህዝብ ከጥላቻ ወጥቶ ይቅርታን እንዲማር አደርገዋል ። ለአለም ይቅርታን ያስተማሩ ፣ ፍቅርን የሰብኩ እና የጸናት ተምሳሌት የነበሩት እኚሁ ሰው በዛሬው ቀን ከ 9 አመት በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-05