ሀገሬ ቲቪ

65 በመቶ የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ቀጠና መራቃቸው ተነገረ

ከትግራይ ኃይሎች 65 በመቶው ከውጊያ ቀጠና መራቃቸው ተገለጸ። በፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት እና የናይሮቢው የትግበራ ሰነድ መሰረት የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ቀጠና እንዲርቁ መደረጉን የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ገልጸዋል።

ጄነራሉ ሰራዊቱን ከጦር ግንባሮች የማራቅ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ለትግራይ ቴ.ቪ. ገልጸዋል። የተንቀሳቀሰው የሰራዊቱን ትክክለኛ ቁጥር ባይጠቅሱም ከፍተኛ ኃይል መሆኑን የተናገሩት ጄኔራሉ ከጦር ግንባሮች በመኪናና በእግር ማንቀሳቀስ መቻሉንም አስረድተዋል።

ከጦርነት ቀጠናዎች ከማራቅ በተጨማሪ ወደተመደበላቸው ቦታዎችም መስፈራቸውንም ተናግረዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-12-05