ሀገሬ ቲቪ

የዩክሬይን ስንዴ የያዘች መርከብን ለኢትዮጵያ ላከች

ዩክሬይን በሰብዓዊ ፕሮግራሟ ስንዴን የያዘች መርከብን ለኢትዮጵያ ላከች። ይህችው መርከብ ለኢትዮጵያ 25 ሺህ ቶን ስንዴን ይዛ ጂቡቲ ዶራሌህ ወደብ መድረሷን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የዘለንስኪ ቢሮ አስታውቋል።

የፕሬዝዳንቱ ቢሮ መግለጫ እንዳስታወቀው ዩክሬይን ሌሎች 60 መርከቦችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ እና የመን የመላክ እቅዶች እንዳሏት ጠቁሟል።

በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 336 ሺህ ቶን የግብርና ምርቶችን የያዙ ዘጠኝ መርከቦች ከዩክሬይን ኦዴሳ ወደብ መነሳታቸውንም ዩክሬይን አስታውቃለች።

በአብርሃም በለጠ
2022-12-05