
የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የቀጠናውን ሰላም ለመጠበቅ የሚያስችል የሰላም አስከባሪ ሃይል ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደረሱ።
ይህም ስምምነት በቀጠናው የሚስተዋለውን ጽንፈኝነትን እና ሽብርተኝነትን ለመከላከል እንዲሁም በየሃገራቱ የሚከሰቱ መፈንቅለ መንግስት ጣልቃ በመግባት ለማስቀረት የሚያስችላቸው መሆኑን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
የቀጠናው ሃገራት ያላቸው የመከላከያ ሃይል እስካሁን ሽብርተኝነትን ከመከላክል አኳያ ደካማ የነበረ ሲሆን አሁን የሚያቋቁሙት ይሄው የሰላም አስከባሪ ሃይል የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ከማስጠበቅ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
በማህሌት አማረ
2022-12-05