ሀገሬ ቲቪ

የአውሮፓ የነዳጅ መግዣ ውሳኔ

የምዕራባውያን የነዳጅ መግዣ ዋጋን ቆረጡ። ከዛሬ ጀምሮ የሩሲያን የተፈጥሮ ጋዝ በበርሜል ከ60 ዶላር በታች በሆነ ዋጋ ብቻ እንደሚገዙ ይፋ አድርገዋል።

ይህም የመድን ተቋማት እና የብድር አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች የሚሰጡት አገልግሎት፤ ሩሲያ ለቡድን ሰባት አባል ሀገራት እና ለአውሮፓ የምትሸጠው ነዳጅ ከዚህ ዋጋ በታች ከሆነ ብቻ እንዲሆን የሚያደርግ ነው።

ሀገራቱ ይህንን ቢሉም ሩሲያ የተፈጥሮ ጋዟን ለአውሮፓውያን መሸጥ ማቆሟ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔያቸው በአለም የነዳጅ ገበያ ላይ የዋጋ አለመረጋግት እንዳይፈጥር ተሰግቷል።

ውሳኔው የሩሲያን ኢኮኖሚ ለምዳከም ነው ቢባልም ሀገሪቱ ግን ምርቶቿን ለቻይናና ህንድ እያቀረበች ነው።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-05