ሀገሬ ቲቪ

ዛሬም ድረስ ሳይጠፋ የሚነደው እሳት

ዛሬ ደግሞ ወደ ዕስያዊቷ ሀገር ጎራ ልንል ወደናል። ከወደዚያ ዓለም ሊያየው የሚጎርፍለት አወይ ተፈጥሮ የሚያሰኝ ግሩም ተዓምር በዚያ አለና።

ይህች ተዓምረኛ ሀገር የዕሳት ምድር ትሰኛለች፤ ምክንያቱ ደግሞ ዛሬም ድረስ አመድ ሆኖ ሳይዳፈን እየተንበለበለ ያለ እሳት በውስጧ አለ እና ነው።

ከዚህኛው እንጀምርላችሁ ይህ በ17 ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባ ቤተ መቅደስ ነው በውስጡ ያለው ይህ እሳት ዛሬም ድረስ ሳይጠፋ የእሳቱ አመድነት ሳይታይ መዝለቅ ችሏል።

ይህ የእሳት ቤተመቅደስ በተፈጥሮ ጋዝ ቦታ ላይ ተሰርቷል ይላሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች። በዚያ ቤተመቅደስ በየጥጉ ሰብሰብ ያሉ ድንጋዮች ያለማቋረጥ ሲነዱ እስተዋላል።

የሀገሬው ሰው ያናር ዳግ ይለዋል፣ የእሳቱ ተራራ ማለት ነው። ተራራው ያለማቋረጥ ዛሬም ድረስ ይንቦለቦላል። በተለይ ቱሪስቶች በማታ ይህንን የእሳት ተራራ መመልከት እና መሞቅን ይሻሉ። የተለየ ስሜትን ይፈጥራል ባዮችም በርካቶች ናቸው።

ምንም እንኳን እሳቱ መንደድ ከጀመረ ከመቶ ያለፈ ዓመታት ተቆጥረዋል የሚሉ ቢኖሩም አንዳንዶች ኝ እሳቱ በ1940 ዎቹ ዓ.ም. መንደድ መጀመራቸውን ይናገራሉ።

ታዲያ በዚህ ይህ እሳት እንዴት ሊገኝ ቻል? ሳይጠፋ ዘመናትን ሊሻገር ቻለ? ለሚሉ ጥያቄዎች ተመራማሪዎች መልስ አለን ባዮች ናቸው።

የዚህ እሳት መነሻው ሚቴን የተሰኘው የጋዝ አይነት ነው ይላሉ። ከተራራው በታች ይህ ጋዝ በስፋት በመኖሩ ተራራውን እየመገበ የእሳት ተራራ አሰኝቶታትል ሲሉም ይናገራሉ።

ታዲያ በአዘርባጃን ዘመናትን የተሻገረው የሚነደው ተራራ አመዱ ሳይታይ ዛሬም ድረስ የበርካቶችን ልብ እያሸፈተ አለ።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-05