ሀገሬ ቲቪ

“በወለጋ አስቸኳይ አዋጅ ይታወጅ” የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ዜጎች ም/ቤት

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ዜጎች ም/ቤት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን በንጽሁን ላይ የደረግሰውን እልቂት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ም/ቤቱ በተደጋጋሚ በአማራነታቸው ሕይወት እየተመነዘረ የዜጎች ፍትሀዊ የመኖር ዓለም አቀፋዊ መብቶች በዘር በተደራጁ ቡድኖች መጣስ የለበትም በቃ ሊባል ይገባል ብሏል።

ስለዚህም የፌደራል መንግሥቱ በወለጋ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አሳስቧል።ከሚሰራው ግፍ ጀርባ ያለው ም/ቤቱ ኦነግ ሲል የጠራው ነውና መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድበት በመግለጫው አሳስቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-06