8ኛው የኢትዮ- ሩስያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ስብሰባው በሁለቱ አገራት መካከል በኢኮኖሚ፣በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ተግባራዊ በምታደርጋቸው የምጣኔ ሃብት አማራጮች ላይ የራሺያ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።
በኢትዮጵያ የራሽያ አምባሳደር ኢቨገንሲ ተርክኒን በበኩላቸው በመድረኩ የተደረጉ ስምምነቶችን በተግባር ለመቀየር፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለመጨመር ምክክር እንደሚደርግም አንስተዋል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-06
