አልጀሪያ ለስፔይን የምታቀርበውን የተፈጥሮ ጋዝ እንደምታቋርጥ አስጠነቀቀች። እንደፎሬይን ፖሊሲ መረጃ አልጀሪያ በ2021 ብቻ 43 በመቶ የሚሆነውን የስፔይን የጋዝ ማስገባት ድርሻ ይዛለች። አሁን ታዲያ ከተስማማነው ውጭ ወደ ሆነ አቅጣጫ የምልከው ጋዝ ከተላከ የምልከውን ጋዝ አቋርጣለሁ ስትል ስፔይንን አስፈራርታለች። ለስፔይን የምትልከውን ጋዝ ልታቋርጥ እንደምትችል ያስጠነቀችው ከሞሮኮ ጋር ባላት ውጥረት ሳቢያ ነው ተብሏል።
በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28
