የፊንላንድ መንግሥት ኔቶን መቀላቀል የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ለሀገሪቱ ፓርላማ መላኩን ሲጂቲኤን ዘግቧል። ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም የ አብል ልሁን ጥያቄ ለኔቶ ማቅረቧ የሚታወስ ነው።
ፊንላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ፓርላማው ሪቂቅ አዋጁን በሚገባ እንዲያጤነው በቂ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው ብሏል።
የኔቶ አባል ከኾኑ 30 ሀገራት ውስጥ 28ቱ የፊላንድን ጥያቄ የተቀበሉ ሲኾን ተርኪዬ እና ሀንጋሪ ግን ውስኔአቸውን እስካሁን አላሳወቁም ተብሏል።
በተመሳሳይ ስዊድንም አባል ለመኾን እየተጠባበቀች ትገኛለች።
በሙሉጌታ በላይ
2022-12-06
