ሀገሬ ቲቪ

የናሳ ተመራማሪዎች ከማርስ የተነሱ ምስሎችን ያጋሩበት ቀን

ከፕላኔቶች ሜርኩሪን ብቻ በመብለጥ ሁለተኛዋ ትንሽ ፕላኔት ናት ። ማርስ ። በተለምዶ ቀይዋ ፈለክ እየተባለች የምትጠራው ይቺ ፕላኔት ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት በአብዛኛው በካርቦንዳዮክሳይድ የተሞላች እናዲሁም ድንጋያማ በመሆኗ ለሰው ልጅ መኖሪያ ምቹ አይደለችም ይላሉ ።

ታዲያ የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ( ናሳ ) ከዛሬ 16 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ማርስ ግሎባል ሰርቬይየር በተባለው የጠፈር መንኮራኩር በመታገዝ ከናሳ ምስሎቾን አንስቶ መላክ ችሎ ነበር ።

ከፕላኔቷ የተነሱት ምስሎችም በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በማርስ ላይ ወይም በአካባቢዋ ፈሳሽ ውሀ እንደሚኖርና በወቅቱም ባልታወቁ ቦታዎች ላይ እንዳለ ፍንጭ የሰጡ ነበሩ።

ማርስ ግሎባል ሰርቬይየር የተባለው መንኩራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማርስ የተጓዘው ኅዳር 7, ቀን 1996 ነበር ። ማንኩራኩሩ ከአንድ ቶን በላይ የሚመዝን ሲሆን የማርስን የሙቀት መጠን መለካት የሚያስችል ስፔክትሮሜትር ፤ የፕላኔቷን ገጽታ በካርታ ላይ ለማውጣት የሚረዳ ሌዘር አልቲሜተር እንዲሁም ፤ በውስጧ ያሉ ነገሮችን የሚያነሳ ከፍተኛ መጠን ያለው ካሜራ ይዞ ነበር ።

የጠፈር መንኩራኩሩ ወደ ማርስ ከተጓዘ ከ 10 ወራት በኋላ ከማርስ በላይ ከፍተኛ ክብ ቅርጽ ያለው ምሕዋር መኖሩን አረጋገጠ ። ማንኩራኩሩ የሄደበትን ተልዕኮ በሂደት እያሳካ ቢሆንም ከጠፈር መንኮራኩሮቹ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በአንዱ ላይ የተፈጠረው ችግር ሂደቱን በማራዘም ዋነኛ የካርታ ተልዕኮውን ከአንድ ዓመት በላይ እንዲዘገይ አስገድዶታል ።

ወደጠፈረው የተላከው መንኩራኩር ማርስ ላይ ሥራውን ባከናወነባቸው የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ስለ ፕላኔቷ ከዚህ በፊት ተሰብስበው ከነበሩት የተሻሉ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን በማግኘት ለዐለም አጋርቷል። በማርስ ወቅታዊ ዑደት ላይ ያለው ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታም በጥናት ተረጋግጧል ።

ማርስ ግሎባል ሰርቬይየር ከሄደባቸው ተልኮዎች አንዱ የሆነውን የፕላኔቷን ገጽታ በምስል ማስቀረት በጎርጎሮሳዊያኑ 2006 በዛሬዋ ቀን በማከናወን አጋርቷል ።

ናሳ ያጋራው ምስልም ፕላኔቷ ላይ ውሀ ሊኖር እንደሚችል የጠቆመ ሲሆን ይህም ከዚህ በፊት በነበሩት ተልኮዎች ላይ ባለመስተዋሉ ብዙዎችን አስገርሞ ነበር ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-06