ዘመኑ ብዙዎች የሌሎችን ለመንጠቅ በሚተጉበት በዚህ ዘመን ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈለኝ ነው ያለው አየርላንዳዊ ብዙዎችን አስገርሟል።
የባቡር ጣቢያ የፋይናንስ አስተዳደር ሰራተኛው ያለምንም ስራ በወር ደሞዝ መቀበሌ ተግቢ አይደለም እንደውም የተናቅሁ ያህል ይሰማኛል ብሏል። ሳይሰራ ይከፍለኛል ያለውን ተቋም ፍርድቤት ገትሯል።
በየጊዜው ከሚለዋወጠው የኑሮ ውድነት አንፃር በየጊዜው ደመወዝ ይጨመረን ጥያቄ የሚያነሱ እና ከሚሰሩበት መስሪያቤት እንዲሁም መንግስት ጋር በየጊዜው እሰጣገባ ውስጥ የሚገቡ ሰራተኞችን መስማት የተለመደ ነው።
ከወደ አየር ላንድ የተሰማው ግን ከዚህ እጅጉን ተቃራኒ ነው በትክክል ስራየን ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው በማለት የሚሰራበተን መስሪያቤት ፍርድ ቤት ገተሮታል ።
ነገሩ ምን መሰላቸሁ በአየር ላንድ ብሄርዋኢ የባቡር ጣቢያ ፋይናንስ ሃላፊ ከ2ሺ ዓመተ ምህርጥ ጀምሮ እስከ 250 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ባጀት ላይ የመውስን ሽLታን የንበረው ሰው ነበር ።
ከ2008 የኢኮኖሚ መዋዠቅ በኋላ ግን የጣቢያው የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀየሩና የርሱም የስራ አድርሻ እየቀነስ መጣ ይባሱን ብሎ እርሱን የሚመለከት አንዳችም ስራ ከዋናው መስሪያቤት አልደርሰው አለ።
እረፍት ወጥቶም ስራው እስኪስተካከል በሚል ቆይቶ ቢመጣም የተለውጠ ነገር የለም። እርሱ እንደሚለው ሁሌ እመጣለሁ ቢሮዬ ገብቼ ኢሜሊን ሰመልለከት አንዳች እኔን የሚመለከት ስራ የለም ስለዚህ የገዛሁትን ጋዜጣ ሳነብ እና በየስዐቱ ትኩስ ነገርና ምግቤን ስበላ ውዬ እሄዳለሁ። መስሪያቤቱ አንዳች ሳልሰራ በየአመቱም 130 ሺ የአሜሪካን ዶላር ደሞዝ ይከፍለኛል ይህ አግባብ አይደለም ባይ ነው ሰውዬው።
ዴርሞት አልስታየር እንደሚለው ባልፉት ዘጠኝ አመታት የባቡር ጣቢያው የፋይናንስ አስተዳደር ብሆንም የሁል ጊዜ ተግባሬ ግን ዘ ታየም እና ኢንዲፔንዳንት የተሰኙ ሁለት ጋዜጦችን እንዲሁም ሳንዱች ገዝቼ ወደ ስራ ገበታየ እሄዳለሁ።
ቢሮየ ከገባሁ በኋላ ከስራ ጋር የተገናኙ ኢሜሎች ካሉ አያለሁ ብዙ ጊዜ አይኖሩም ቀኑን ሙሉ ጋዜጣ እያነበብኩ እና ሳንዱች እየበላሁ አሳልፋልሁ ከዚያም አሰር አሰት ተኩል አካባቢ ኢሜሌን በድጋሜ አያለሁ የተላከልኝ ነገር ካለ አይና እመልሳለሁ። በሳምንት አንዴ እንኳ እኔን የሚጠይቅ ስራ ካለ ደስታየ ወደር የለውም በደስታ እሰራለሁ ።
አሁን ግን ይህ አክሄድ ሰልችቶኛል ሳይሰሩ መብላትም ተገቢ ስላልሆን ተቋሜን ከስሻለሁ ብሏል።
ሳልሰራ መከፈሌ ወንጅል ነውም ባይ ነው ። መስሪያቤቴ ባለሙያ እንደመሆኔ መጠን በችሎታየ እና በእውቀቴ መጠቀም ነበረበት። በደንብ ስራ ሊሠጠኝ ሲገባ እኔን ያለ ስራ ደመወዝ መክፈሉ ንቀት ነው ለዛም ነው ፍርድቤት የገተርኩት ይላል።
ፍርድቤቱም የሚልስን አቤቱታ በሚገባ ተቀብሎ ምላሽ ለመስጠት ለየካቲት ቀጠሮ ሰጥቶታል። የስውን ለመቀማት ብዙዎች በሚጥሩበት በዚህ ዘመን የተከፈልኝም ያልሰራሁትን ነው ይሚል ሃቅኛ ሲገኝ ምን ይሉታል ያብዛህ እንጂ።
በማህሌት አማረ
2022-12-06
