ሀገሬ ቲቪ

መቀሌ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌትሪክ ሃይል ማግኘቷ ተገለጸ

ከሁለት አመታት በላይ በዘለቀው ግጭት ከመብራት አገልገሎት ውጭ የነበረቸው መቀሌ የኤሌትሪክ አገልግሎት እያገኘች መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበኩሉ የመቀለ ኤሌክትሪክ መስመር ከብሔራዊ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግሪድ ጋር መገናኘቱን በትናትናው ዕለት አስታወቆ ነበር ።

በግጭቱ ከመሰረታዊ አገልገሎቶች ወጪ የነበሩት ትግራይ ክልል ከተሞች የመብራት እንዲሁም የቴሌ ኮም አገልግሎቶች የተጀመሩ መሆኑ መረጃው አመላክቷል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-07