
ኢትዮጵያን ጨምሮ 17 የአፍሪካ ሃገሮች አንድ ወጥ የሆነ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በሙከራ ደረጃ ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ።
ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኮትዲቯር እና ካሜሮንን ጨምሮ በሙሉ ንብረትነታቸው የአፍሪካ የሆኑ አየር መንገዶች ከአንዱ አገር ወደ ሌላው በሚያደርጉት በረራ የነበሩባቸውን ገደቦች የሚያስቀር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስታዉቋል፡፡
ይህ ገበያም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መልካም ዕድል ይዞ የሚመጣ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በማህሌት አማረ
2022-12-07