ሀገሬ ቲቪ

በኮንጎ መንግስትና በታጣቂዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኤም 23 በተባለው ታጣቂ ቡድን መካከል በናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ሶስተኛ ዙር የሰላም ውይይት መጠናቀቁ ተገለጸ ።

በኮንጎ መንግስትና በታጠቁ ሀይሎች መካከል በተደረገው ውይይት ተስፋ ሰጪ ስምምነቶች መፈረማቸውን የቀድሞ የ ኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ አስታውቀዋል ።

በስምምነቱ መሰረት የታዩት መሻሻሎች ጥር ወይም የካቲት ላይ የአፈጻጻም ሪፖርት እንደሚቅርብላቸውም ገልጸዋል።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኤም 23 ታጣቂዎች ከ100 በላይ ንጹሀን መገደላቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት መናገራቸው ይታወሳል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-07