በጆርጂያ ሲወዳደሩ የነበረሩት ራፋኤል ዎርኖክ አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ ዲሞክራቶችን በሴኔት አብላጫውን መቀመጫ ያዙ ።
ዎርኖክ ከሪፕብሊካኑ ተወካይ ኸርሸል ዎልከር የገጠማቸውን ከባድ ፉክክር በበላይነት ማሸነፉቸውን ተከትሎ ዲሞክራቶች በአሜሪካ ምክር ቤት ያላቸውን የመቀመጫ ቁጥር ከፍ አድርገዋል።
በዚህም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፓርቲያቸው በላይኛው ምክር ቤት 51 ለ 49 በሆነ ውጤት እየመራ ይገኛልል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በባለፈው ወር በአሜሪካን በታችኛው ምክር ቤት ጥቂት ወንበሮችን ብቻ በመያዛቸው ዲሞክራቶች ዝቅተኛ ግምት ተሰጥቷቸው እንደነበር ይታወሳል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-07
