ሀገሬ ቲቪ

ሞሶሎኒ የተገደለበት ዕለት

የዛሬዋ እለት ከ77 አመታት በፊት የጣሊያኑ አምባገነን ቤኒቶ ሞሶሎኒ እና እመቤቱ ክላራ ፔታሲ የተገደሉባት ሆና አገኘናት። ሙሶሎኒ ጣሊያንን ለ20 አመታት በአምባገነንነት አስተዳድሯል። በፈረንጆቹ 1945 የሁለተኛው አለም ጦርነት አቅጣጫ ተቀይሮ ሽንፈት በነጀርመን እና ጣሊያን ላይ ሲሆን ጥንዶቹ ቤኒቶ ሙሶሎኒ እና ክላራ ፔታሲ ወደ ስዊዘርላንድ ለመሸሽ ሞከሩ። ግና የጥንዶቹ ሞታቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ በያዛቸው አንድ ጣሊያናዊ ወታደር ተኩስ ሆነ።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28