ሀገሬ ቲቪ

የነፍስ አድን ድሮን

ቴክኖሎጂዎች የሰውን ልጅ የኑሮ ዘይቤ የማቅለያ መሳሪዎች መሆን ከጀመሩ አመታትን አስቆጠርዋል ።

የድሮን ቴክኖሎጂዮች ታዲያ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰዎች በፍጥነት በማይደርሱባቸው አከባቢዎች በመድረስ ለሆስፒታሎች የደም አቅርቦትን ሲያደርሱ እንዲሁም ለተለያየ ተግባራት የሚውሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሲቀርጹ እና የተለያዩ መልክቶችን ለሰዎች በየቤቱ ለማድርሰ ሲንቀሳቀሱ መመልከት የተለመደ ሆኗል ።

ታዲያ እነዚህ የድሮን ተግባራት በአሁን ወቅት በውሃ ዳርቻ መስጠም አደጋ ላይ ለሚገኙ ሰዎች መፈትሄ ሆነዋል ተብሏል ።

በፈረንጆች አቆጣጠር 2021 በእንግሊዝ የሮያል ነብስ አደን ሰራተኞች 3 ሺ የሚሆኑ ሰዎችን በወሃ ዳርቻ ከመስጠም አደጋ ቢታደጉም ከመቶ የሚበለጡ ሰዎች ግን ለሞት ተዳርገዋል ።

በውሃ ወስጥ እየስጠሙ የሚገኙ ሰዎች በአብዛኝው ህይወታቸው የሚያለፈው የነብስ አድን ሰራተኞች እስኪደርሱ ባለው ሰአት በሚጠፋው ግዜ ወስጥ ነው ።

ይህን ችግር ያቀላል እንዲሁም ሰዎችን በቶሎ ይታደጋል በማለት የሮያል የህይወት አድን ማህበር የነበስ አድን ድሮኑን በመጠቀም አገልገሎት ሙከራ ጀምሯል ።

ድሮኑ አይ ፒ (IP 67) ይባላል ይህን ድሮን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ ውኃ የማያሰገባ ፣ እንዲሁም በዘናብ ሆነ በአስቸጋሪ ነፋስ ወስጥ መጓዝ የሚያስቸለው ቴክኖሎጂ የያዘ በመሆኑ ነው ።

ድሮኑ የአደጋ ጠሪ ወደ በደረሰበት አካባቢ የህይወት አድን መንሳፈፊያ በመያዝ አደጋው በደርሰበት አከባቢ በማቅናት በመስጠም አደጋ ውስጥ ለሚገኘው ሰው የነብሰ አድን መንሳፈፊያወን ያቀበላል ።

መንሳፈፊያው የደረሳቸው ሰዎች ታዲያ በምንሳፈፊያው ላይ በመሆን ለተጨማሪ እርዳታ የነብስ አድን ሰራተኞችን ይጠበቃሉ የነብስ አድን ሰራተኞች በታው በመድረስ እርዳታ የሚሰፈልገውን ሰው ።

በተለይ የዚህ የነብስ አድን ድሮን ተግባር ይፍጸማሉ ። ይህ ቴክኖሎጂ ታዲያ ወደ ተለያዩ አውሮፓ ሃገራት ሰደተኞች በባህር ላይ ለሚገጠማቸው የመስጠም አደጋ መፍትሄ መሆን ይችላል ተበሎለታል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-07