ሀገሬ ቲቪ

ኢሰመኮ በወለጋ ለተፈጠረው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች ኦነግ ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች ናቸው አለ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወለጋ ዞኖች ባጋጠመው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች ኦነግ ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች ናቸው አለ ።

የኢሰመኮ የምርምርና ክትትል ሪጅናል ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “በሰላማዊ ዜጎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ውስጥ በዋነኝነት ኦነግ ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው” ብለዋል።

የምርምር እና ክትትል ዳይሬክተሩ አክለውም ከሰሞኑ የተፈጸሙት ጥቃቶች መጠን ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችልም ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ባለፉት ቀናት የደረሱትን የጉዳት መጠን ለማወቅ ማጣራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-07