ሀገሬ ቲቪ

ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች የማስወገድ ሥራ ተጀመረ

የሕክምና፣ የግብርና፣ የምርምር እና ሌሎች የሥራ ዘርፎ የተለያዩ ኬሚካሎችን ለሥራ ግብአትነት ይጠቀማሉ። እነዚህ ኬሚካሎች ታዲያ የመጠቀሚያ ጊዜአቸው ካለፈ ጉዳትን የሚያስከትሉ በመኾናቸው ‘’አደገኛ ቆሻሻ’’ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡ በርካታ ኬሚካሎች ውስጥ አንዱ የኾነው ለጤናው ዘርፍ የሚያገለግለው ዲዲቲ የተሰኘ ኬሚካል እንደኾነ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ጀነራል ግርማ ገመቹ ተናግረዋል።

ጊዜው ያለፈበትን 1400 ቶን የዲዲቲ ኬሚካል የማስወገዱ ሥራ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ በዓለም አቀፍ ሁኔታዎች እንደዘገየ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን መናገሩ የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ በአዳማ የኬሚካሎች ማከማቻ መጋዘን የሚገኘውን የዲዲቲ ኬሚካል የማሸጉ ሥራ እንደተጀመረ ሰምተናል።ከዚህ ቀደም ደግሞ አዳሚ ቱሉ በሚገኘው መግዘን ታሽጎ ለጉዞ ዝግጁ የኾነውን ኬሚካል ወደ ሚወገድበት ሀገር ለመላክ ዝግጁ መኾኑን ነው አቶ ግርማ የነገሩን በሁለት ወራት ውስጥም ሥራው ይጀመራል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-08