ሕዳር 29 1962 ዓ.ም በተማሪዎች ንቅናቄ ወስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የብሔሮች እኩልነት ቦታ ይኖረው ዘንድ ትልቅ አስተዋጻኦ የነበረው አንድ ወጣት በወቅቱ ሀገሪቷን ሲመራ በነበረው የቀ/ኃ/ሥ መንግሥት የተገደለበት ዕለት ነው። ይህ ወጣት ዋለልኝ መኮንን ይባላል።
ዋለልኝ መኮንን በወሎ ክ/ሀገር አማሀራ ሳይንት ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ 1939ዓ.ም ነበር የተውለደው ። የአንደኛ ደረጃ ትምሕርቱን በደሴ ከተማ ንጉስ ሚካዔል አንደና ደረጃ /ቤት ሁለተና ደረጃ ት/ት ደግሞ በወ/ሮ ስህን ት/ቤት አጠናቋል። በ1950 መጨረሻ አካባቢ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴን ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የፖለቲካ ሳይንስ ት/ቱን ተከታትሏል።
ጊዜው በወቅቱ የነበሩ ተማሪዎች እና ወጣቶች የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴን መንግሥት በመሬት ላራሹ እና በሌሎች የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ወጥረእው የያዙበት ነበር። የዚህ ትግል አንድ አካል የነበረው ዋለልኝም ብዙ ጊዜ ከት/ቱ ታግዷል ወደ ወኀኒ እንዲወርድም ተደርጓል።
የተማሪዎች ንቅናቄ ከተፈጠረ ከአስር ዓመት በላይ እስኪኾነው ድረስ ይፋ ያልወጣ የብሄር እኩልነት ጥያቄን ዋለልኝ መኮንን ይፋ አደረገ። ይህ ጥያቄው የወቅቱን መንግሥት ቁስል የነካ እንደነበር ክፍሉ ታደሰ ያትውልድ በሚለው መጽሐፋቸው ገልጸዋል
በዚህ ትግል ውስጥ የነበረው ዋለልኝ መኮንን በ1964ዓ.ም አውሮፕላን በመጥለፍ ከሀገር ውጪ ለመውጣት ከ 6 ጉዳደኞቹ ጋር ያደረገው ሙከራ በደኀንነት ኃይሎች ቀድሞውኑ ታውቆ ነበር እና በተወሰደባቸው እርምጃ ከ 51 ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት ተገድሏል።
ዋለልኝ በሀገሪቱ ያሉ ብሔረሰቦች እኩል ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው በማቀንቀን ይታወቃል። በዚሁ ዕለት ሕዳር 29/1987 የጸደቀው የኢፌድሪ ሕገመንግሥት ሕገ መንግሥት ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ሲንከባለል የመጣውን የብሔር እንኩልነት ጥያቄ አንኳር ጉዳዩ አድርጎ እንደጽደቀ ይነገርለታል። በዚህ ኃሳብ የማይስማሙ በርካታ ሰዎች መኖራቸው እንዳሉ ኾነው። ከዚያ ባሻገር ሕዳር 29 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እየተከበረበት ዛሬ ላይ 17ኛ ዓመቱን ይዟል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-12-08
