ጠቅላይ ሚንስትሩ በሐዋሳ በተካሄደው 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ቤት ያለምሶሶ ፣ ማገርና ጣሪያ እንደ ማይቆም ሁሉ ኢትዮጵያም ሁሉንም ብሔር ብሔረስቦች በአንድነትና በእኩልነት ማጣመር ስትችል ዘላቂነቷ ይረጋገጣል ብለዋል።
ታሪክን ዛሬም የግጭት መንሳኤ ማድረግ ትተን ለመማሪያ ከተጠቀምንበት የትሻለ ነገን ለመስራት አቅም እንድሚሆንም ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።
በስሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ሂደት ይበልጥ ስኬታም አእንዲሆን መንግስት የሚጠበቅበትን ሁሉ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።
ሁሉም ዜጋ በሁሉም ቦታ እንደፈለገ የሚኖርባትን ሀገር ለመስራት የጋራ ጥረት ማደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-12-08
