ሀገሬ ቲቪ

ኢዜማ በአዲስ አበባ በሚገኙ ት/ት ቤቶች የተፈጠሩ ግጭቶት እየተባባሰ ሊሄድ ይችላል አለ

ኢዜማ የአዲስ አበባን ሕዝብ መብትና ፍላጎት በጉልበት ለመጨፍለቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም ሲል ጠየቀ ።

ፓርቲው ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ፣ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፣ የክልል መለያ አርማና መዝሙርን መነሻ በማድረግ አላስፈላጊ ውጥረትና ግጭት እንዲቀሰቀስ እና የትምህርት ሂደቱ እንዲስተጓጎል ተደርጓል ብሏል ።

በዚህም በርካታ ተማሪዎች እና መምህራን ለእስር መዳርገአቸውንም ገልጿል። ሁኔታውም እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶችም አሉ ሲል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አመላክቷል ።

ፓርቲው በት/ቤቶች በተነሱ ግጭቶች የተነሳ ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። ለእስር የተዳረጉት ተማሪዎች እና መምህራን በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል።

በማህሌት አማረ
2022-12-08