ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱማሊያ ያለው ድርቅ ከዚህ ሊከፋ ይችላል አለ

የተባበሩት መንግስታት ድርጀት እና የአረብ ሊግ ሃገራት ባደረጉት ስብሰባ በሱማሊያ እየቀጠለ የሚገኘው ድርቅ አደገኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲል አስጠንቅቀዋል ።

ሱማሊያ በተደጋጋሚ ጊዜ እየገጠማት የሚገኘው የዝናብ እጥረት በሃገሪቱ ለተከስተው ደርቅ ምክንያት ሆኗል ተበሏል ።

በሱማሊያ ከአጠቃላይ 15 ሚልዮን ህዝብ ግማሽ ያህሉ በድርቅ ሳቢያ በምግብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኝ ተጠቅሷል ።

1.3 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል ። በቀጣዩ አመት መጨረሻም 6.7 ሚሊዮን ሕዝብ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊገጥማቸው ይችላል ሲሉ ተመድ እና የአረብ ሊግ ሃገራት ሰጋታቸውን ገልጸዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-08